ዶ/ር በረከት አማኑኤል :እየሠራሁበት ከነበረ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ የግንባታ ታታሪ ጉልበት ሠራተኞች ደሞዝ በቀን 700-1000 የሚከፍላቸው ሲሆን ከጤና ባለሙያዎች ይልቅ ከ2-3 እጥፍ ነው።
ለነሱ ከዚህ በላይ ቢከፈልም ደስተኛ ነኝ ነገር ግን ... ይጋጫል!
አንድ ሐኪም 2 ደቂቃ ዘጎይቶ ከሆነ አዲስ የተወለደ ሕፃን መተንፈስ መጀመር ባለመቻሉ ይሞታል
ለ 3 ደቂቃዎች ዘግይቶ ቢመጣ አንድ እናት ከወሊድ ጋር በተያያዘ ደም መፍሰስ ትሞታለች
አንድ ዶክተር ለ5 ደቂቃ ከዘገየ ትንታ እና የአየር ቧንቧ መዘጋት የሚገላቸው አሉ
አንድ ዶክተር ለ 7 ደቂቃ ቢቆይ ድንገተኛ የልብ ድክመት ብዙ ሰው ይገላል
አንድ ሐኪም ለ 10 ደቂቃ የሚዘገይ ቢሆን የሚጥል በሽታ እና በሰውነት መንቀጥቀጥ(seizure) ይሞታል
ለ 15 ደቂቃ ያህል ዘግይቷል ቢገኝ ራሱን ስቶ የሚሞተው ሰው ብዙ ነው
ሐኪሙ ለ 30 ደቂቃ ቢቆይ አለርጂ ወይም anaphlaxis በቀላሉ መግደል ይችላል.
አንድ ሐኪም ለአንድ ሰዓት ያህል ቢዘገይ የድንገተኛ ክፍል ታካሚዎች መዳን የሚችሉት ሳይቀሩ ላይመለሱ ያሸልባሉ።
ለዶክተሮች እያንዳንዷ ስብርባሪ ሰኮንድ ህይወት ናት ዋጋዋ።
በየደቂቃው የሚተርፈው የሰው ሕይወት ዋጋ ቢስ ካልሆነ በስተቀር ለየሚፈውሱ እጆች ባለምጡቅ አይምሮ ዶክተሩ ምንም ቢያንስ እንጂ አይበዛበት.
Via ዶ/ር በረከት አማኑኤል MD ደራሲየ IYE [Influential YouthEthiopia] መስራች እና ስራ አስኪያጅ,