Event

ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር

Advertisement

ሐምሌ 26 የት ኖት?

ፍኖት ማኅበረሰባዊና ሥነ-ልቡናዊ የምክክር የበጎ አድራጎት ድርጅት በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በመዝገብ ቁጥር 4683 የተመዘገበ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡

በሀገራችን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውሶች በዜጎች ላይ አለመረጋጋትን፣ ጭንቀትን፣ ተስፋ መቁረጥን እያስከተሉና የሕዝባችንን ደኅንነት አደጋ ላይ እየጣሉ በመሆናቸው ፍኖት መፍትሔው ላይ እየሠራ ይገኛል፡፡

ፍኖት የቤተሰብ መበተንን የብዙ ማኅበራዊና ሥነ-ልቡናዊ ችግሮች መንስኤ እንደሆነ ያምናል፤ ለዚህም ትዳርና ቤተሰብ ላይ እንዲሁም የአእምሮ ጤና ላይ ልዩ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ይገኛል፡፡ ሕጋዊ ዕውቅና አግኝቶ ከተቋቋመበት ከ2012 ዓ.ም ጀምሮም በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች አገልግሎት ሰጥቷል፡፡

አገልግሎቱን እየሰጠ የሚገኘውም በበጎ ፍቃደኝነት የተሰባሰቡ አባላቱን በማስተባበር ሲሆን ይህንኑ ተደራሽ ለማድረግ እገዛን ይሻል፡፡ ለዚህም ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ቦሌ ብራስ በሚገኘው ዮድ አቢሲኒያ የባሕል ምግብ አዳራሽ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ የገቢ ማሰባበሰቢያ መርሐ ግብር አዘጋጅቷል፡፡

በዕለቱም ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት አካላት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና መገናኛ ብዙኃን ይገኛሉ፡፡ እርስዎም በዕለቱ ተገኝተው ፍኖት የያዘውን ትውልድን የማዳን ተግባር በመደገፍ፤ ጤናማና ጽኑ ማኅበረሰብ የመፍጠር ርዕዩን በጋራ ዕውን እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል፡፡

እንዲሁም ድርጅቶች ስፓንሰር በማድረግ የፍኖት ቤተሰብ እንድትሆኑና ምርትና አገልግሎታችሁን እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።

#በፍኖት
#በፍኖት መንገድ በጋራ ለለውጥ
#ተስፋ ከመቁረጥ ወደ ብርሃን



Advertisement
Share with someone you care for!

Best of Addis Ababa Events in Your Inbox