የምስጋና ኮንፍራንስ ጷጉሜ 2/2016 ዓ.ም, 14 August | Event in Addis Ababa | AllEvents

የምስጋና ኮንፍራንስ ጷጉሜ 2/2016 ዓ.ም

BeEthiopia YeMedihanealem Tehadiso Church Mission Department

Highlights

Thu, 14 Aug, 2025 at 03:00 am

Idoro,

Advertisement

Date & Location

Thu, 14 Aug, 2025 at 03:00 am (EAT)

Idoro

Addis Ababa, Ethiopia

Save location for easier access

Only get lost while having fun, not on the road!

About the event

የምስጋና ኮንፍራንስ ጷጉሜ 2/2016 ዓ.ም
የኮንፍራንሳችን ሶስተኛ ቀን
ቅዳሜ ጷጉሜ 2/2016 ዓ. ም
ዝማሬ: በወጣቶች እምልኮ ቡድን

የቃሉ አገልጋይ: ወንጌላዊ ሻሎም አስፋው
ርዕስ:በእግዚአብሔር የሚጠበቅ ምስጋናና የአመስጋኙ ሕይወት
ክፍለ ምንባብ: መዝ. 49(50):1-23

መግቢያ:እግዚአብሔር በመጀመሪያ ስለማንነቱ የሚመሰገን አምላክ ነው። በመቀጠል ስለሰራው ሥራ እግዚአብሔር መመስገንን ይሻል።ይህንን በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እናገኛለን።
መዝ. 28(29):1-2 መዝ 112:1-9

ዋና ዋና ነጥቦች
1. ከቁጥር 1-6 የሚናገረው እግዚአብሔር ሕዝቡን ለወቀሳ ሲጣራ ማነቱን በማስተዋወቅ ይጀምራል።
-ክፍሉ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ መሆኑን በመግለጽ ከማደሪያው በግልጽ እንደሚመጣ እና ዝምም እንደማይል ዘማሪው ይናገራል።
- እግዚአብሔር ፈራጅ ደግሞም ፍርዱም ትክክል እንደሆነ ሰማያት እንኳን ይመሰክራሉ።
'ሚልክያስ 3:3 - ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያነጻ ሰው ይቀመጣል፤ ሌዋውያንንም አንጽቶ እንደ ወርቅና እንደ ብር ያጠራቸዋል፤ ከዚያም እግዚአብሔር ቊርባንን በጽድቅ የሚያቀርቡ ሰዎች ይኖሩታል፤'

2. ሰማይና ምድርን ለምስክር ይጠራል። 7
እግዚአብሔር ሕዝቡን ሊዘልፍ ሲወርድ ሰማያትንና ምድርን ለምስክርነት ይጠራል።

'ኢሳይያስ 1:2 - ሰማያት ሆይ፤ ስሙ ምድር ሆይ፤ አድምጪ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናግሮአልና፤ “ልጆች ወለድሁ፣ አሳደግኋቸውም፤ እነርሱ ግን ዐመፁብኝ።'

3. እግዚአብሔር ሕዝቡን ይወቅሳል፣ይዘልፋል 7-23

ሀ.ምስጋናን ስላጓደሉ እግዚአብሔር ለወቀሳ ወረደ ቁ.14
እግዚአብሔር ከሕዝቡ የሚቀርብለትን መስዋዕት፣ ስጦታና ቁርባንን አላጣም። በዚህም ለወቀሳ አልወረደም። የእርሱ መሻት የምስጋና መስዋዕትን እንዲያቀርቡለት ብቻ ነው። ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ጉደለት በሚያቀርቡት መስዋዕት የሚሞሉና የእነርሱ ጥገኛ አስመስለውት ነበር። ይህንን ለመዝለፍ ወረደ።

'መዝሙር 50:8 - 14 ስለ መሥዋዕትህ አልነቀፍሁህም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህማ ሁል ጊዜ በፊቴ ነው።...ብራብ ለአንተ አልነግርህም፤ ዓለምና በውስጧ ያለውም ሁሉ የእኔ ነውና።... ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕት አቅርብ፤ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ።'

ለ. ሕዝቡ በግብዝነት ተስበው ስለነበር እግዚአብሔር ይወቅሳል። ቁ. 16
'መዝሙር 50:16-19 ክፉውን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፤ “ሕጌን ለማነብነብ፣ ኪዳኔንም በአፍህ ለመናገር ምን መብት አለህ ...ሌባውን ስታይ አብረኸው ነጐድህ፤ ዕድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ። አፍህን ለክፋት አዋልህ፤ አንደበትህም ሽንገላን ጐነጐነ።'

ሐ. ሕዝቡ ተግሳጽን የጠላ ስለነበር እግዚአብሔር ዘለፈ። ቁ. 17
መዝሙር 50:17 - ተግሣጼን ትጠላለህና፤ ቃሌንም ወደ ኋላህ ትጥላለህ።'.
የእግዚአብሔር ሕዝብ ጌታን የሚያገለግል ብቻ ሳይሆን በምታልፍ ምድር ላይ አምላኩን አስከብሮ ማለፍ የሚጠበቅበት ሕይወት ነው። ይህንንም እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይጠብቃል፣ለዚያም ይሰራል።
እግዚአብሔር መመስገን የሚሻ አምላክ ነው። ምስጋና ደግሞ:
1. እግዚአብሔርን የማክበሪያ መንገድ ነው።
2. እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚያድንበት መንገድ ነው።በመሆኑም እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ አመስጋኝ እንድንሆን ልንወስንና ከኩራታችንና ከትዕቢታችን ለንመለስ ይገባል።

interested
Stay in the loop for updates and never miss a thing. Are you interested?
Yes
No

Ticket Info

To stay informed about ticket information or to know if tickets are not required, click the 'Notify me' button below.

Advertisement

Nearby Hotels

Idoro,, Addis Ababa, Ethiopia

Just a heads up!

We have gathered all the information for you in one convenient spot, but please keep in mind that these are subject to change. We do our best to keep everything updated, but something might be out of sync. For the latest updates, always check the official event details by clicking the "Find Tickets" button.

Get updates and reminders
Advertisement
የምስጋና ኮንፍራንስ ጷጉሜ 2/2016 ዓ.ም, 14 August | Event in Addis Ababa | AllEvents
የምስጋና ኮንፍራንስ ጷጉሜ 2/2016 ዓ.ም
Thu, 14 Aug, 2025 at 03:00 am